Ethiopia Immigration Services and Importance Notice

Immigration Services
Ethiopia Immigration Office provides three major services to the Ethiopians and the International community. These services include Tourist visas, business visas, transit visas, and students visa. The Ethiopian immigration also provides registration of vital events of Ethiopian citizens. So, learn more about the services of Ethiopia Immigration from our website.
Importance Notice to all Ethiopian Passport Applicants
Because of starting online passport services, illegal dealers have been increasing from time to time, both in Addis Ababa and regional cities. Such illegal dealers do not fill the applicant’s information with quality. In addition, they request higher service charges from the applicants. Sometimes, they also fill in their own contact information instead of the customer’s contact phone, thus the applicants cannot receive the confirmation text messages.
Moreover, some illegal dealers misleading online passport applicants by creating a similar website. When applicants apply for an online passport service from illegal websites, both information and the payment go to illegal individuals. Ethiopia Immigration office is also providing such important notice to the applicants of Ethiopia Immigration services.
Therefore, all customers and Ethiopians should know about such illegal activities and dealers when they request Ethiopian immigration services. Moreover, we all are responsible to share such important notice with our friends.
የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አገልግሎት
የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አገልግሎት
የተለያየ ጥናቶች እንደሚያመለክተው ከስምንት አገራት ማለትም ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቱኒዚያ፣ አልጄሪያ፣ ኬፕ ቨርድ፣ ሳዎቶሜና ፕሪንሲፔ፣ ሲሼልስ እና ሞሪታኒያ ባስተቀር፤ 50 የአፍሪካ ሃገራት የሞት መመዝገቢያ ሥርዓት የላቸውም። በአውሮፓ ሃገራት ደግሞ ከአልባኒያ እና ሞናኮ በስተቀር ሁሉም አገራት ዓለም አቀፋዊ የሞት ምዝገባ ሥርዓት አላቸው። እንዲሁም በእስያ ከግማሽ በላይ አገራት የሞት መመዝገቢያ ሥርዓት እንዳላቸው የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያሳያል።
የዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አገልግሎት በኢትዮጵያ ህጋዊ አሰራር ተከትሎ የከተማውን ሕዝብ ልደት፣ ጋብቻ እና ሞት በክብር መዝገብ የጀመረው በ1934 ዓ.ም ነው፡፡ በተጨማሪ በ1952 ዓ.ም የወጣው የፍትሕ-ሐብሔር ህግ ውስጥም የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን ለመዘርጋት ተብለው በርካታ አንቀጾች እንዲካተቱ ተደርገዋል፡፡ እንዲሁም ማዘጋጃ ቤቶች፣ የከተማ አስተዳደር ጽ/ ቤቶች፣ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ እና የጤና ተቋማት ወሳኝ ኩነቶችን የተመለከቱ ምዝገባዎች የማካሄድና መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራዎች እንዲካሄዱም ተደርጓ ነበር፡፡ ስለዚህ በ1935 ዓ.ም የጋብቻ፣ በ1946 ዓ.ም የልደት፣ በ1962 ዓ.ም የሞት ምዝገባ ጀመረ፡፡
ከ1983 ዓ.ም ወዲህ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ዘመኑ ከደረሰበት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተጣጣመና በየጊዜው እየጎለበተ እንዲሄድ ለማድረግ የሚያስችል ስራዎች እንዲሰራ ለማድረግ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በ2010 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚያስገኘው ጠቀሜታ አንጻር ትኩረት ተሰጥቶት ከወሳኝ ኩነት ጋር በመዋሀድ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ጉነት ኤጀንሲ በሚል ስያሜ እንደ አዲስ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አሰራሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና አለም የደረሰበት ሁኔታ ጋር አሰራሩን እያዘመነ ወቅቱ የሚጠይቀውን አደረጃጀት በመፍጠር ዘመናዊ የኢሚግሬሽን አሰራር በመከተል ቀደም ሲል በማንዋል ፖስፓርት ይሰጥ የነበረውን በማስቀረት ኤሌክትሮኒካል ፖስፓርት መስጠት እንዲጀመር ማድረግ ተችሏል፡፡
የኢሚግሬሽን አገልግሎት
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- የቪዛ አገልግሎት መስጠት – የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የቱሪስት ቪዛ፤ የቢዝነስ ቪዛ፤ የትራንዚት ቪዛ እና የተማሪ ቪዛ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኝ ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑት፡፡
- የፓስፖርት አገልግሎት መስጠት – አዲስ ፓስፖርት፤ ምትክ ፓስፖርት እና የፓስፖርት እድሳት አገልግሎቶች ለዜጎች ይሰጣል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኝ ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑት፡፡
- የወሳኝ ኩነቶች አገልግሎት መስጠት – ዜጎች የልደት፤ የጋብቻ እና የሞት ምዝገባ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኝ ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑት፡፡
ለፓስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች በሙሉ
የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የፓስፖርት አገልግሎትን ተገልጋዬች የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኝት በሚችሉበት ቦታ ሆነው ጊዜና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በኦንላየን ምዝገባ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በመሆኑ ዜጎች በማንኛውም በአካባቢያችሁ ባለ የኢንተርኔት አገልግሎት ከሞባይል ስልክ ወይንም ከኮምፒዩተር በመጠቀም www.ethiopianpassportservices.gov.et የሚለውን ሊንክ በመግባት በእራስዎ ወይንም በሌላ ቅርብ የቤተሰብ አባል ወይም በጓደኛዎ ድጋፍ በመሙላት ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ክፍያዎትንም የሚፈፅሙት በባንክ በኩል ስለሆነ ቀጠሮ ለመያዝ ወደ ኤጀንሲው ቢሮ በአካል መምጣት ሳያስፈልግ በባንክ መክፈል ይችላሉ፡፡
በፓስፖርት አገልግት የህገ-ወጥ ድርጊቶች
የበይነ መረብ ወይም ኦንላየን የፓስፖርት አገልግሎት እንሰጣለን የሚሉ ህገወጥ ድርጅቶችና ግለሰቦች አዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ እነዚህ ድርጅቶችና ግለሰቦች ያለአግባብ የአገልግሎት ክፍያን ከመጨመር በላይ የተገልጋዩን መረጃ በጥራት አይሞሉም፡፡ እንዲሁም የተገልጋዩን መረጃ በሚሞሉበት ጊዜ የራሳቸውን ስልክ ቁጥር በተገልጋዩ መረጃ ላይ በመሞላት ለተገልጋዩ ተገቢው የፅሁፍ መልእክት እንዳይደርሰው ያደርጋሉ፡፡
Related Topics
- How can apply online to Ethiopia Immigration?
- Birth, Marriage and Death Registration in Ethiopia
- How to apply for Ethiopian Passport online
- የኢትዮጵያ ፓስፖርት አገልግሎት በኦንላይን ለማውጣት
ሌላኛ የህገ-ውጥ ተግባር ደግሞ ተመሳሳይነት ያለውን ድህረ ገጽ በማዘጋጀት፤ አመልካቾች ለኦንላይን የፓስፖርት አገልግሎት እንዲያመለክቱ ማድረግ ነው፡፡ ተመሳሳይነት ባላቸው እንዲህ ዓይነት ድህረ ገጾች አመካይነት አመልካቾች በሚያመለክቱበት ጊዜ፤ መረጃውም ክፊያው ወደ ህገወጥ ግለሰቦች ይሄዳል፡፡ ለዚህም ማሳሰቢያ እንዲሆን የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ መረጃ ለተጠቃሚዎች እያደረሰ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ሁሉም የፓስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች እና ሌሎች የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን የሚትጠቀሙ በሙሉ እንደዚህ ዓይነት ህገ-ወጥ ተግባራት እንድትጠነቀቁና ለሌሎችም መረጃውን እንድታደርሱ ይሁን፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳይ የገጠማችሁ ተገልጋዮች ካላችሁ ልምዳችሁን ለሌሎችም ጭምር ያድርሱ፡፡ ወይም በኮሜን መስጫ ይፃፉ፡፡
ሠላም
ፖስፖርት ለማደስ ፈልጌ ፎርሙን ኦን ላይን ሞልቼ ከጨረስኩ በኃላ መጨረሻ ላይ ብር ላይ 1200 ብር አለኝ ክፍያ ደሞ የሰማውት 600 ብር ነው ስለዚህ እኔ ያወጣውት 2013-2018 በፈረንጆች አቆጣጠር ነበር ግን ሦስት ዓመት አልፎኛል ሳላድሰው መጨጫ አለው ወይ
2. በፊት ሳወጣ የልደት ካርድ አይጠይቅም ነበር አሁን የግድ የልደት ሠርተፍኬት ካርድ ያስፈልገኛል ወይ ለማደስ
በተጨማሪ ድሮ ያወጣውት በልደታ ክ/ከተማ ነበር አሁን ግን መታወቂዬ የካ ነው የሚለው ማለት ቦታ ቀይሬ ነው ችግር አለው ወይ
can you give me the correct link to fill the form online so that I renew my passport?
enamesegnalen
i have paid at CBE and can’t get confirmation txt within 2hour
please would you contact immigration officer?
when the e visa will open again
It has no clear deadline but you can apply on your respective country’s Embassy.
i have paid at CBE mobile banking and can’t get my passport till now the appointment say aug 23 today is 29
በመጀመርያ ቀጠሮ ፎቶና አሻራ ለመስጠት ስሄድ የግድ የታደሰ የቀበሌ መታወቅያ ያስፈልጋል አሁን ባለው ሁኔታ ደሞ ቀበሌ መታወቂያ አይሰጥም ጊዜያዊ ደሞ መታወቅያ ላለው ሰው አይሰጥም ታዳ ይሄ ነገር እንዴት ነው?
የይህ ሊንክ http://www.ethiopianpassportservices.gov.et አይሰራም፡፡ ፓስፖርት ለማደሰስ በጣም ተቸግረናል፤ የትኛውን እንጠቀም ?
የመታወቀያ አለመታደስም ሌላው ችግር ነውና እባካችሁ መፍትሄውን ንገሩን፡፡
Comments are closed.